ሊሮይ ሳኔ ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ከተቀነሰ በኋላ ምን አለ?

ጀርመናዊው ወጣት የመስመር ተጫዋች የሆነው ሊሮይ ሳኔ በአለም ዋንጫው ጀርመንን ከሚወክሉት ተጫዋቾች ውጪ ከሆነ በኋላ የተሰማውን ስሜት ገልፇል።

በማን ሲቲ በአመቱ 14 ጎሎችን በማስቆጠር እንዲሁም ለቡድኑ የፕሪምየርሊጉ ሻምፕዮንነት ጉልህ ሚና ከተጫወቱት ውስጥ የሚጠቀሰው ሊሮይ ሳኔ በአለም ዋንጫው ላይ አንመለከተውም።

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዩአኪም ሎው ተጫዋቹን ከቀነሱት በኋላ ባለፉት ሁለት ቀናት መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ተጫዋቹ ካሳለፈው የተሳካ የውድድር አመት የተነሳ በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ መካተት እንደነበረበት የሚናገሩ በዝተዋል።

ሌሎች በበኩላቸው የአሰልጣኙ ውሳኔ ሊከበር እንደሚገባው እና ሀላፊነቱም የአሰልጣኙ መሆኑን በመግለፅ ውሳኔውን ተቀብለውታል።

ተጫዋቹ ከብሔራዊ ቡድኑ ውጪ ከሆነ በኋላም በጣም መከፋቱን ቢያሳውቅም ለቡድኑ ግን ውጤታማ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልፇል።

“ትናንት እና ዛሬ የማበረታቻ መልእክት ለላካችሁልኝ በሙሉ አመሰግናለው።ግልፅ ነው በአለም ዋንጫ ባለመሳተፌ ተከፍቻለው ነገርግን ይህን ውሳኔ ተቀብዬ ለቀጣዩ ጠንክሬ ሰርቼ ወደ ቡድኑ ለመመለስ አስባለው።ለቡድኑም መልካም ምኞት እመኛለው።ሂዱና ዋንጫውን አሸንፉ!”የሚል መልእክት አስተላልፏል።

Advertisements