ማንችስተር ዩናይትድ የክረምቱ ሁለተኛ ፈራሚውን አሳወቀ

ማንችስተር ዩናይትድ የብራዚላዊውን ፍሬድ ዝውውር ማጠናቀቁን ባሳወቀ ከ24 ሰአት በኋላ የክረምቱን ሁለተኛ ፈራሚውን አሳወቀ።

የፖርቶው የቀኝ መስመር ተከላካይ የሆነው ዲየጎ ዳሎት የዩናይትድ ሁለተኛ ፈራሚ መሆኑ ተረጋግጧል።

የ19 አመቱ ወጣቱ ተጫዋች በፖርቶ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ወደ ዋናው ቡድን ከመጣ በኋላ ስምንት ጨዋታዎች ላይ ተሳታፊ ሆኗል።

ተጫዋቹ በሁለቱም መስመሮች መከላከል የሚችል ሲሆን በተለይ የአንቶኒዮ ቫሌንሺያ የወደፊት ተተኪ የመሆን አቅም እንዳለው ተነግሯል።

ዩናይትዶች ለተጫዋቹ 17.4 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ በማድረግ ለአምስት አመት አስፈርሞታል።የኮንትራት ውሉም ለስድስ አመት የማራዘም እድልም ሊኖር እንደሚችል ተነግሯል።

ተጫዋቹ ከዝውውሩ በኋላ “ማንችስተር ዩናይትድ መቀላቀል ለኔ የማይታመን አጋጣሚ ነው።” ሲል ተናግሯል።

have grown up in Porto’s academy and I am so thankful for everything they have done for me. But the chance of coming to the biggest club in the world is something I just couldn’t turn downጆሴ ሞሪንሆ በበኩላቸው ዲዮጎ በጣም ችሎታ ያለው በክለቡ በፍጥነት ታላቅ ተጫዋች መሆን የሚችል ወጣት ተከላካይ ነው።
አንድ የመስመር ተከላካይ ሊኖሩት የሚገባው በሙሉ የያዘ ነው።በሱ እድሜ ክልል እሱ በአውሮፓ ምርጡ ተከላካይ ነው። ሁላችንም ከፊትለፊቱ ብሩህ የሆነ ጊዜ እንደሚጠብቀው እናምናለን።” በማለት ተናግረዋል።