1994 አሜሪካ – አይረሴ የአለም ዋንጫ የደሰታ አገላለጾች

1994 ላይ የተደረገው 15ኛው የአለም ዋንጫ በወቅቱ በእግርኳስ በቅጡ በማትታወቀው የአሜሪካ ግዛቶች የተደረገ እንደነበር ይታወሳል፡፡

አሜሪካ ሽርብትን ብላ ያስተናገደችው ውድድር በታላቅ ድምቀት ሲካሄድ በውድድሩ ሊረሱ የማይችሉ ትዝታዎችን ጭሮ አልፏል፡፡ከዚህ ውስጥ ከአእምሮ የማይጠፉ አስደናቂ የደስታ አገላለጾች ይገኙበታል፡፡

1)ቤቤቶ፣ሮማሪዮ እና ማዚንሆ

የውድድሩ አሸናፊ የሆነችው ብራዚል ሆላንድን 3-2 ባሸነፈችበት ጨዋታ ቤቤቶ ግብ ጠባቂውን አልፎ ያስቆጠራት ድንቅ ጎል ከቡድን ጓደኞቹ ጋር በመሆን ደስታውን የገለጸበት መንገድ አሁንም ድረስ በአለም ዋንጫው ከማይረሱ የደስታ አገላለጾች አንዱ ነው፡፡ 

ተጫዋቹ አዲሱን ልጁን እንኳን ደህና መጣህ በማለት ሁለት እጁን ዘርግቶ “እሽሩሩ” ሲል ታይቷል፡፡ይህ በወቅቱ የተወለደው የቤቤቶ ልጅ ኦሊቬራ አሁን 24 አመቱ ሲሆን ከፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር አጭር ቆይታ ካደረገ በኋላ ለቪቶሪያ ጉማሬዝ እየተጫወተ ይገኛል፡፡

2) ራሺድ ያኪኒ

የ 1994 ድንገተኛ ድንቅ ቡድን ሆና ብቅ ያለችው በአለም ዋንጫው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው የአፍሪካዊቷ ተወካይ ናይጄሪያ ነበረች፡፡

ናይጄሪያ በጣሊያን በአሳዛኝ ሁኔታ ከውድድሩ እስከተሰናበተችበት ድረስ የነበራት ድንቅ ብቃት አይዘነጋም፡፡

በተለይ ቡልጋሪያን በገጠመችበት ጨዋታ በአለም ዋንጫው የመጀመሪያ ጎል ለናይጄሪያ ያስቆጠረው ራሺድ ያኪኒ መረብ ውስጥ እጁን በማስገባት በስሜት ደስታውን የገለጸበት መንገድ ፈጽሞ አይዘነጋም፡፡

3)ፊኒዲ ጆርጅ

አፍሪካዊያን ለየት ያለ የደስታ አገላለጽ በማሳየት እንደሚታወቁ ያረጋገጠበት ሌላው አጋጣሚ በዚሁ የአለም ዋንጫ ላይ ናይጄሪያ ግሪክን ስትገጥም ፊኒዲ ጆርጅ ያሳየው የደስታ አገላለጽ ነበር፡፡

ፊኒዲ ጎሉን ካስቆጠረ በኋላ በጉልበቱ በመንበርከክ እና እግሩን እንደ ውሻ ከፍ በማድረግ(Doggy Style) ያሳየው የደስታ አገላለጽ ሌላው የ 1994ቱ የማይረሳ አጋጣሚ ነበር፡፡

ይህ የደስታ አገላለጽ ከዛ በኋላ የተለያዩ ተጫዋቾች እየተገበሩት የሚገኝ ሲሆን በቅርቡ እንኳን የናፖሊው ድረስ መርተንስ የዚህ አይነት የደስታ አገላለጽ ማሳየቱ ይታወሳል፡፡

የአለም ዋንጫ ትዝታዎች ይቀጥላሉ…

Advertisements