ሉሲዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከአልጄሪያ አቻቸው ጋር አድረገው ተሸነፉ

በጋና አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2018 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ሉሲዎቹ ከአልጄሪያ አቻቸው ጋር አድርገዋል።

ባለሜዳዎቹ የአልጄሪያ የሴት ብሔራዊ ቡድን ሴኔጋልን በማሸነፍ ለመጨረሻው የማጣሪያ ፍልሚያ መብቃት የቻሉ ሲሆን ሉሲዎቹ በበኩላቸው ሊቢያ ላይ የጎል ዝናብ በማውረድ 15-0 ማሸነፋቸው አይዘነጋም።

ሁለቱ ቡድኖች ምሽት 6:00 ላይ በስታድ ዱ 5 ጁላይ ስታድየም ያደረጉት ጨዋታ በባለሜዳዎቹ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ሉሲዎቹ 15ኛ ደቂቃ ላይ በረሂማ ዘርጋ አማካኝነት ጨዋታውን ቀድመው መምራት ቢችሉም የነበረባቸው የተከላካይ ክፍተት እና የቡድን ውህደት ማጣት ሶስት ጎሎችን አስተናግደው ተሸንፈዋል።

በተለይ 32ኛ ደቂቃ ላይ አሲያ ሲዱም፣ቡሄኒ እና ቤን ላዛር ባማረ እንቅስቃሴ የሉሲዎቹን ግብ ጠባቂ ንግስት መአዛን በማለፍ ሲዱም ያስቆጠረችው ጎል ድንቅ እንቅስቃሴ የታየበት ነበር።

ሌሎቹን ጎሎች 19ኛው ደቂቃ ላይ ረመዳኒ እንዲሁም ከእረፍት መልስ ፋቱማ ሴኩዋኔ ያስቆጠሯቸው ጎሎች ናቸው።

የመልሱ ጨዋታ ከሶስት ቀናት በኋላ በአአ ስታድየም የሚከናወን ሲሆን የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የምሽቱን ጨዋታ የመቀልበስ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል።

ነገርግን በመልሱ ጨዋታ ጎል ሳያስተናግዱ 2-0 እና ከዛ በላይ ማሸነፍ የሚችሉ ከሆነ በድምር ውጤት አሸናፊ በመሆን ለጋናው የአፍሪካ ዋንጫ የሚያሳትፋቸውን ትኬት መቁረጥ ይችላሉ።

በሌሎች ጨዋታዎች

ጋምቢያ 0-1 ናይጄሪያ

አይቮሪኮስት 2-2 ማሊ

ኮንኮ 0-5 ካሜሮን

ኬኒያ 2-1 ኢኳቶሪያል ጊኒ

ዛምቢያ 0-1 ዚምባቡዌ

ሌሴቶ 0-1 ደ/አፍሪካ

በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።

Advertisements