1994 አሜሪካ – ጆርጅ ካምፖስ [ኤል ብሮዲ]

የ1994ቱ የአለም ዋንጫ በወቅቱ እግርኳስ በማትታወቀው አሜሪካ ቢካሄድም እንደተገመተው ሳይሆን ውድድሩ በከፍተኛ ተመልካች እና በደመቀ መልኩ መከናወኑ አይዘነጋም።

የተለያዩ የማይረሱ አጋጣሚዎች ያሉት ይኸው የአሜሪካው የአለም ዋንጫ እስካሁን ድረስ ሊታወሱ የሚችሉ ሁነቶችን አስተናግዶ አልፏል።

ከዚህ ሁስጥ ለዛሬ ያሰናድናላችሁ የሜክሲኮው ግብ ጠባቂ ጆርጅ ካምፖስ [ኤል ብሮዲ] የተመለከተ ይሆናል።

የእግርኳስ ህይወቱን አጥቂ ሆኖ የጀመረው እና በመቀጠል በግብ ጠባቂነት ለሀገሩ መሰለፍ የቻለው ካምፖስ በ1994ቱ የአለም ዋንጫ ላይ አድርጎት ይጫወትበት በነበረው መለያ ይታወሳል።

ተጫዋቹ በወቅቱ እራሱ ዲዛይን እንዳደረገው ሲነገር የነበረው መለያው ደማቅ እና የተለያየ ቀለም ያለው ስለነበረ በቀላሉ እይታ ውስጥ ይገባ ነበር።

በተለይ በተክለ ሰውነቱ አነስ ያለ ስለነበር ያደርገው የነበረው ማሊያ ሰፊ እና ከሰውነቱ ጋር የማይስማማ እንደነበር ይታወሳል።

በአንድ ወቅት ስለ መለያው ቀለም ምርጫው የተናገረው ካምፖስ ልብሶችን ዲዛይን ማድረግ እንደሚወድ እንዲሁም የሚጠቀማቸው የመለያ ቀለሞች በሜክሲኮ የፓስፊክ ውቅያኖስ ጠረፍ ላይ የምትገኘው በሚኖርባት አካፑልኮ ከተማ የሚገኘው የባህር ዳር የአሸዋ መዝናኛ[A beach Resort] ላይ በብዛት የሚለበስ ቀለም እንደሆነ ገልፆ ነበር።

ተጫዋቹ በቁመቱም እንደ ሌሎች ግብ ጠባቂዎች ረጅም ሳይሆን 1.68 ሜ ብቻ የሚረዝም በመሆኑ አንዳንዴ ከቡድን አጋሮቹ ጋር የሚነሳው ፎቶ ረጅም ለመምሰል በጣቱ ቆሞ ተንጠራርቶ ፎቶ ይነሳ ነበር።[ምስሉን አስተውለው ይመልከቱት]

ትንሹ ካምፖስ አጀማመሩ አጥቂ ሆኖ ስለነበር አሁን Goal Keeper እንደሚባለው ሁሉ ግብ ጠባቂ ሆኖ ሲጫወት ከጎል ክልሉ ወጥቶ በእግሩ በመጫወት ይታወቅ ነበር።

የሜክሲኮ ብሔራዊ ቡድንን የሚያስታውሱ እግርኳስ ወዳጆች ብላንኮ፣ራፋኤል ማርኬዝ፣ጆቫኒ ዶ ሳንቶስ እና ቺቻሪቶን እንደሚያስታውሱ ሁሉ የ1994 ቱን የአለም ዋንጫ የተመለከቱ ደግሞ ጆርጅ ካምፖስን ፈፅሞ አይዘነጉትም።

ግብ ጠባቂው ሜክሲኮን ወክሎ በ 1994፣1998 እና በ 2002 የአለም ዋንጫ ላይ መሳተፉ ይታወሳል።

Advertisements