አርጀንቲና ማኑኤል ላንዚኒ በጉዳት ከአለም ዋንጫው ውድድር ውጪ መሆኑን አሳወቀች

​የዌስትሀሙ አርጀንቲናዊው ኮከብ የሆነው ማኑኤል ላንዚኒ ዛሬ ጠዋት ልምምድ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ከአለም ዋንጫው ውጪ መሆኑ ታውቋል።

ተጫዋቹ ጉልበቱ ላይ ያጋጠመው ጉዳት ረዘም ያለ የማገገሚያ ጊዜ እንደሚፈልግ የታወቀ ሲሆን በፕሪምየርሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ላይም ለዌስትሀም የመድረሱ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል።

ተጫዋቹ በሆርጌ ሳምፓኦሊ 23 ተጫዋቾችን ያካተተው የቡድን ዝርዝር ውስጥ ተካቶ የነበረ ቢሆንም ጉዳቱ ቡድኑን እንዳያገለግል አድርጎታል።

ቡድኑ በላንዚኒ ምትክ ሌላ ተጫዋች ለመተካት የሚገደድ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግን ተተኪው ተጫዋች ማን እንደሆነ አልታወቀም።

ቡድኑ ግብጠባቂው ሰርጂዮ ሮሜሮን በተመሳሳይ በጉልበት ጉዳት ከሳምንት በፊት ያጣው መሆኑ ይታወሳል።

አርጀንቲና በአለም ዋንጫው የመጀመሪያዋን ጨዋታ ከአይስላንድ ጋር በማድረግ የምትጀምር ሲሆን በመቀጠል ከክሮሺያ እና ከ ናይጄሪያ ጋር የምትጫወት ይሆናል።

Advertisements