1994 አሜሪካ -የማይረሱ የተጫዋቾች ስታይሎች

አሜሪካ አዘጋጅታው የነበረው የ 1994ቱ የአለም ዋንጫ በውድድሩ ላይ ከታዩ ሁነቶች በተጨማሪ ተጫዋቾች ይዘውት የመጡት የፀጉር እና የፂም ስታይሎች ቀልብ ስበው እንደነበር ይታወሳል።

1) አሌክሲ ላላስ (ቀዩ ኮርማ)

አሜሪካዊው ተከላካይ አሌክሲ ላላስ በ 1994 ሀገሩ አዘጋጅታው በነበረው የአለም ዋንጫ ላይ አሳይቶት የነበረው
የፂም እና የፀጉር ስታይሉ ፈፅሞ አይዘነጋም።

ይህ የሙዚቃ ተጫዋች ፂሙን እንደ ፍየል ወደ ታች አስረዝሞ ፀጉሩንም እንዲሁ አሳድጎ የተለየ መልክ ይዞ መጥቶ ነበር።ላላስ አሁን ከ ፎክስ ስፖርት ጋር እየሰራ ይገኛል።

2) ሮቤርቶ ባጂዮ

የ1994 ቱ የአለም ዋንጫ መልከመልካሙ ጣሊያናዊው ሮቤርቶ ባጂዮ ለአዙሪዎቹ ድብልቅልቅ ያለ ስሜትን ፈጥሮ አልፏል።

ቡድኑን ለፍፃሜ በማብቃት ትልቅ ሚና ቢጫወትም በፍፃሜው ጨዋታ ከብራዚል ጋር በመለያ ምት ሲለያዩ የመጨረሻውን ኳስ በተለምዶ “አሞራ ሲያይሽ ዋለ”አጠራር ከላይኛው አንግል በላይ በላካት ኳስ ጣሊያን መሸነፏ ይታወሳል።

ባጂዮ ከዚህ በተጨማሪ በውድድሩ ሊታወስ የሚችልበት የነበረው የፀጉር ቁርጥ ስታይሉ ነበር።

ፀጉሩን ከኋላ በማርዘም ያሳየው ስታይል በብዙ እንስቶች ጭምር በፍቅር መማረክ ችሎ ነበር።

በሀገራችንም ከዛን ጊዜ በኋላ የተጫዋቹን የፀጉር ስታይል በተለይ በልጆች ላይ በሰፊው የታየ ሲሆን አሁንም በአንዳንድ ቦታዎች ተመሳሳይ አይነት ቁርጦች መታየታቸውን አላቆሙም።

Advertisements