1994 አሜሪካ – በአንድ ጨዋታ ሁለት ሪከርዶች

2.jpg

እንደ አሁኑ ሳይሆን በቀደሙት የአለም ዋንጫዎች አፍሪካዊያን የሚኮሩበት የማይበገሩት አንበሶች በሚባሉት በካሜሮን ብሔራዊ ቡድን ነበር።ነገርግን በ 1994ቱ የአለም ዋንጫ ለካሜሮናችም መልካም ትዝታን ጭሮ ማለፍ አልቻለም።


በምድባቸው የመጨረሻ ጨዋታ ላይ ሶቭየት ህብረት ከፈራረሰች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው ራሺያ ካሜሮንን 6-1 ደቆሰቻች።የሚገርመው ራሺያ የምድቡን ቀድማ ያደረገቻቸው ሁለት ጨዋታዎች በብራዚል እና በስዊዲን በመሸነፏ ካሜሮን ላይ ጎል ማዝነቧ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ በቂ ሳይሆንላት በመቅረቱ በጊዜ ወደ ሀገሯ ተመለሰች።

ይኸው 6-1 የተጠናቀቀው ጨዋታ ግን በእለቱ ሁለት ሪከርዶችን በመስራት እስከ ዛሬ ድረስ በታሪክ መዝገብ ላይ ሰፍሯል።

1.jpg

ኦሊግ ሳሌንኮ

ሳሌንኮ በዚህ 6-1 በተጠናቀቀው ጨዋታ ላይ ካሜሮን ላይ አምስት ጎሎችን በማስቆጠር እስካሁን ድረስ በአለም ዋንጫ ላይ በአንድ ጨዋታ አምስት ጎሎችን በማስቆጠር ሪከርድ ይዟል።

ተጫዋቹ በአለም ዋንጫ ታሪክ ከምድቡ ማለፍ ሳይችል [ሶስት ጨዋታዎችን ብቻ በመጫወት]ነገርግን የውድድሩ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ በመሆንም ሌላ ሪከርድ መስራት የቻለ ብቸኛ ተጫዋች ነው።

ሳሌንኮ በውድድሩ ላይ ስድስት ጎሎችን በማስቆጠር የውድድሩ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ሰባት ጨዋታዎችን ከተጫወተው ከሄሪስቶ ስቶችኮቭ ጋር እኩል ሆኖ ማጠናቀቅ ችሎ እንደነበር ይታወሳል።

ሮጀር ሚላ

ካሜሮናዊው አጥቂ ሮጀር ሚላ በዚህ ጨዋታ ላይ ብቸኛዋን ጎል ለካሜሮን ማስቆጠር ችሎ ነበር።
ተጫዋቹ ይህንን ጎል ሲያስቆጥር እድሜው 42 የነበረ ሲሆን ይህም አንድ ተጨዋች በአለም ዋንጫው በከፍተኛ እድሜ ጎል ያስቆጠረ በመሆን እስከ አሁን ድረስ ሪከርዱን ይዟል።