መሲ፡ ባርሴሎና ለሻምፒዮንስ ሊጉ ግሪዝማን ያስፈልገዋል

ሊዮኔል መሲ አንቱዋን ግሪዝማንን ማስፈረም ለባርሴሎና የሻምፒዮንስ ሊግ ድል ተስፋ “ድንቅ” ነገር መሆኑን ተናግሯል።

የአትሌቲኮ ማድሪዱ ኮከብ ዳጎስ ባለ የዝውውር ሂሳብ ወደኑ ካምፕ እንደሚዛወርና በዚህ ሳምንት ስለወደፊት ዕጣ ፈንታው ለክለቡ በይፋ እንደሚገልፅ ወሬዎች እየተናፈሱበት ይገኛሉ።

እናም ወሬው እውን ሆኖ ግሪዝማን ዝውውሩን የሚያደረግ ከሆነ መሲን፣ ልዊስ ስዋሬዝን እና ኦስማን ዴምቤሌን ያሉ ከዋክብትን በያዘው የባርሴሎና አጥቂ ክፍል ላይ ተጨማሪ ኃይል መሆን ይችላል።

መሲም ከ27 ዓመቱ ፈረንሳያዊ ተጫዋች ጋር በጋራ የመጫወት ያለውን ከፍተኛ ጉጉት ገልፃ ይህም ከ2015 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባርሴሎና በአውሮፓ መድረክ ላይ ድልን መቀዳጅት እንዲችል ትልቅ እገዛ ማድረግ ይችላል ብሎ ያምናል።

“የሻምፒዮንስ ሊጉን ዳግመኛ ማሽነፍ የሚያስችል ተጨማሪ ምርጥ ተጫዋቾች እንደሚያስፈልጉን የሚገልፅ ስምምነት አድርጌያለሁ። ከእነዚያ መካከልም ግሪዝማን አንዱ ነው።” ሲል መሲ ለስፔኑ ስፖርት ጋዜጣ ተናግሯል።

“ክለቡ የሚያስፈርመው ከሆኑ ድንቅ ነገር ነው። የመጀመሪያው ተፈላጊ ተጫዋች መሆኑን አላውቅም። ያ የሚወሰነው በዝውውር ኮሚቴውና በአሰልጣኞቹ ነው።

“እኔ ልል የምችለው ሻምፒዮንስ ሊጉን ለማሸነፍ የግድ ምርጥ ተጫዋቾች የሚያስፈልገን መሆኑ ነው። እናም እሱ በጣም ምርጥ ነው።”

ባርሳ በኤርኔስቶ ቫርቬልዴ የመጀመሪያ የውድድር ዘመን የአሰልጣኝነት ቆይታ ሁለት የሃገር ውስጥ ዋንጫዎችን ቢያሳካም ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ስኬቶች በሻምፒዮን ሊጉ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በሮማ በደረሰበት አሳፋሪ ሽንፈት እንዲደበዝዝ ሆነዋል።

“አይሆንም።” ሲል መሲ ለአህጉሪቱ የውድድር ዋንጫ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ሰጥቶ “ላ ሊጋውን እና ኮፓ [ዴል ሬዩ]ን ማሸነፍ በጣም ወሳኝ ነገር ነው። ቀላል ነገርም አይደለም።

“ምንም እንኳ በሻምፒዮንስ ሊጉ ላይ የተፈጠረው ነገር እንዳለ ቢሆንም፣ የውድድር ዘመኑ በጣም ጥሩ ነበር።

“ከሁለትዮሽ ዋንጫ ጋር ድንቅ ጊዜን አሳልፈናል። ማሸነፉ ትርጉም ስላለው ሻምፒዮንስ ሊጉ ብዙዎችን የሚያስደስት መሆኑ እውነት ነው። ነገር ግን ያደርገነውን ነገር ምንም ነገር ሊያደበዝዝው አይገባም።” ሲል ለዓለም ዋንጫው ውድድር ከአርጄንቲና ጋር ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው መሲ ተናግሯል።