ሞ ሳላህ ከግብፅ ብሔራዊ ቡድን ጋር ልምምድ ጀመረ

ግብፃዊው የሊቨርፑል የአጥቂ መስመር ተሰላፊ የሆነው ሞ ሳላህ ከጉዳቱ አገግሞ ከፈርኦኖቹ ጋር ልምምድ ጀምሯል።

በአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ከሰርጂዮ ራሞስ ጋር እጃቸው ተቆላልፎ መሬት ላይ ከወደቁ በኋላ ሞ ሳላህ ትከሻው ላይ ጉዳት አጋጥሞት ጨዋታውን መቀጠል ሳይችል እያለቀሰ ከሜዳ መውጣቱ ችሏል።

ተጫዋቹ ከጉዳቱ በኋላ ለአለም ዋንጫው የመድረስ እድል እንዳለው ተነግሮ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

ነገርግን መረጃው የብሔራዊ ቡድኑን ተጫዋቾች ለማረጋጋት እንጂ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ተጫዋቹ ወደ ሜዳ የመመለስ እድል እንደማይኖረው በማሰብ ንዴታቸውን በሰርጂዮ ራሞስ ላይ ሲገልፁ የሰነበቱ የፈርኦኖቹ ደጋፊዎችም ነበሩ።

ነገርግን ላለፉት ቀናቶች ህክምናውን ሲያደርግ የነበረው ሳላህ ያሳየው ለውጥ ትልቅ ተስፋ የሰጠ ነበር።

የአለም ዋንጫ የፊታችን ሀሙስ ከመጀመሩ በፊት ሞ ሳላህ ትናንት የግብፅ ብሔራዊ ቡድንን ትናንት ተቀላቅሏል።

ሳላህ ከቡድኑ ጋር ልምምድ የሰራ ሲሆን ከኡራጋይ ጋር ለሚያደርጉት የመጀመሪያ ጨዋታም በአካል ብቃቱ ረገድ ዝግጁ እንደሚሆን ተናግሯል።

ነገርግን የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ሀኪሞች ለመጀመሪያው የአለም ዋንጫ ጨዋታ ተጫዋቹ መድረሱን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ሁለት ቀናት መጠበቅ እንደሚኖርባቸው አሳውቀዋል።

ግብፅ በአለም ዋንጫው የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከምድቡ ጠንካራ ቡድን ከሆነችው ኡራጋይ ጋር የምታደርግ ይሆናል።

በልዊስ ስዋሬዝ የምትመራው ኡራጋይ በበኩሏ በአለም ዋንጫው ቡድኑ በሚጫወትበት ሰአት ትምህርት ቤቶች በሙሉ ተዘግተው የብሔራዊ ቡድኑን ጨዋታዎች እንዲመለከቱ ተፈቅዷል።

Advertisements