ናቢል ፈኪር ወደ ሊቨርፑል ?

የፈረንሳዩ ኦሎምፒክ ሊዮን የቡድኑ አምበል የሆነውን ናቢል ፈኪር ዝውውር ዙሪያ መግለጫ አወጣ።

ስሙ ከሊቨርፑል ጋር በስፋት ተያይዞ የቆየው እና ከአለም ዋንጫው መጀመር አስቀድሞ የቀዮቹ ተጫዋች እንደሚሆን ታስቦ የነበረው ናቢል ፈኪር ዝውውሩ መቋረጡን ሊዮን አሳውቋል።

ተጫዋቹ የፍሊፕ ኩቲንሆ ተተኪ በመሆን ወደ አንፊልድ ለማቅናት ሁለቱ ክለቦች መስማማታቸው ተነግሮ ነበር።

አንዳንድ ድረገፆች እንዲያውም ተጫዋቹ የህክምና ምርመራውን ማጠናቀቁን የሚገልፁ መረጃዎች ይዘው ወጥተው ነበር።

የቀዮቹ ደጋፊዎችም ቡድናቸው እያደረገ ያለው ዝውወር በመደሰት ከወዲሁ በቀጣይ አመት የፕሪምየርሊግ ውድድር ዋንጫ የማንሳት አቅም እንዳላቸው በማህበራዊ ገፆች ላይ ሀሳባቸውን እስከመስጠት ደርሰው ነበር።

ነገርግን ሊዮን ወደ ሊቨርፑል ያቀናል የተባለው የናቢል ፈኪር ዝውውር ከትናንት ምሽት ጀምሮ ማቋረጡን አሳውቋል።

ክለቡ ተጫዋቹ በቀጣይ አመት ከሊዮን ጋር ቆይቶ በቻምፕየንስ ሊጉ ቡድኑን እንደሚመራ አረጋግጧል።

ዝውውሩ ለምን እንደተቋረጠ ባይታወቅም አንዳንድ ዘገባዎች ግን ሊቨርፑል የተጫዋቹን የዝውውር ሂሳብ እንዲቀነስለት በመጠየቁ ነው የሚሉ መረጃዎች ወጥተዋል።

Advertisements