የዕለተ ሰኞ የአውሮፓ የዝውውር ወሬዎች

እንግሊዝ


ማን ዩናይትድ ምባፔን ለማዛወር ተዘጋጅቷል

ማንችስተር ዩናይትድ ለፒኤስጂው ኮከብ ኪልያን ምባፔ ዝውውር ዳጎስ ያለ ዋጋ እያዘጋጀ እንደሚገኝ የስፔኑ ጋዜጣ ዶን ባሎን ዘግቧል።

የጋዜጠው ዘገባ እንዳመለከተው ከሆነም ፒኤስጂዎች ኔይማር ክለቡን የማይለቅ ከሆነ ምባፔን ከክለቡ የመቀነስ ሃሳብ አላቸው። እናም የጆዜ ሞሪንሆው ቡድን ለተጫዋቹ ዝውውር 270 ሚ.ዩሮ ዋጋ ወጪ ለማቅረብ እያጤነበት ይገኛል።

ይሁን እንጂ ዩናይትድ ዋጋውን በማንኛውም ሁኔታ አንቶኒ ማርሺያልን የስምምነቱ አካል በማድረግ ወደ190 ሚ.ዩሮ ዝቅ እንዲል ሊያደርገው ይችላል።

አሊሰን ከዓለም ዋንጫው በፊት የወደፊት ዕጣ ፈንታው መፍትሄ እንዲያገኝ ፍላጎት አለው

ብራዚላዊው ቁጥር 1 ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር የዓለም ዋንጫ ውድድር ከመጀመሩ በፊት የሚኖረው የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዲወሰን ፍላጎት ያለው መሆኑን የጎል ድረገፅ ዘገባ አመልክቷል።

የሮማው ኮከብ ስሙ በከፍተኛ ሁኔታ ከሊቨርፑል የዝውውር ዜና ጋር ተቆራኝቶ ይገኛል። ሪያል ማድሪድም የግብ ጠባቂው ፈላጊ ክለብ መሆኑ ሲገለፅ ቆይቷል።

እናም ግብጠባቂው ቀጣይ ዕጣ ፈንታውን ለወኪሉ አሳልፎ በመስጠት በቀጣዩ የውድድር ዘመን ስለሚጫወትበት ክለብ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ለማወቅ ከፍተኛ ፍላጎት አለው።

ኒውካሰል ራሽፎርድን ለመውሰድ ፈልጓል

የዘሺልድስ ጋዜትሪፓርትስ ዘገባ እንዳመለከተው ከሆነ ኒውካሰል ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ ማርከስ ረሽፎርድን በውሰት ለመውሰድ የሚችልበትን ሁኔታ እየማተረ ይገኛል።

የ20 ዓመቱ የፊት ተጫዋች በቅርቡ ሶስቱ አናብስት ኮስታ ሪካን በረቱበት የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ማራኪ እንቅስቃሴ ማሳየት ቢችልም በኦልትራፎርድ በጆዜ ሞሪንሆ የመጀመሪያ ተሰላፊነት ሚና ሳያገኝ ያለፈውን የውድድር ዘመን አጠናቋል።

በመሆኑም የኒውካሰሉ አሰልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ ራሽፎርድ በዩናይትድ የነበረውን ሁኔታ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በ2018-19 የውድድር ዘመን የተጫዋቹን ብቃት ለማሻሻል የሚችሉበትን ዕቅድ ይዘዋል።

አርሴናል የቴሬራን ስምምነት ለማጠናቀቅ ተቃርቧል

አርሰናል የሳምፕዶሪያውን ተጫዋች ሉካስ ቴሬራን ስምምነት ለማጠናቀቅ መቃረቡን የጣሊያን የህትመት ውጤት የሆነው አንሳ ስፖርትስ ዘግቧል።

ኡራጓዊው ተጫዋች ከክለቡ ጋር የ22 ሚ.ፓውንድ የውል ማፍረሻ የኮንትራት ስምምነት ያለው ሲሆን፣ ሳምፕዶሪያም የሎኮሞቲቭ ዛግሬቡን ላቭሮ ማየርን አስፈርሟል። ይህ ማለት ደግሞ የሴሪ አው ቡድን ከቴሬራ ጋር ለመለያየት ፈቃደኛ ይሆናል ማለት ነው።

ማን ሲቲ ለዳግለስ ኮስታ 100 ሚ.ዩሮ ሊያቀርብ ነው

ማንችስተር ሲቲ ብራዚላዊውን ኮከብ ዳግላ ኮስታን ለማስፈረም በሚያደረገው ጥረት 100 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ዋጋ ለማቅረብ መዘጋጀቱን የፕሪሚየር ስፖርት ቲቪ ዘገባ አመልክቷል።

የክንፍ ተጫዋቹ በ40 ሚ.ዩሮ ለጁቬንቱስ በቋሚነት ፊርማውን ያኖረው በቅርቡ ነበር። ይሁን እንጂ የፕሪሚየር ሊጉ ክለብ ያቀረበው ከፍተኛ ዋጋ የ27 ዓመቱን ተጫዋች ወደማንችስተር ሲቲ እንዲዘዋወር ሊያደርገው እንደሚችል እምነት አለው።

ፒኤስጂ የቼልሲውን ካንቴን ፈልጓል

ቶማስ ቱኸል ፒኤስጂ በዚህ ክረምት የቼልሲውን አማካኝ ንጎሎ ካንቴን እንዲያስፈርም ፍላጎት ያላቸው መሆኑን የእንግሊዙ ጋዜጣ ዘ ሰን ዘግቧል።

የፈረንሳያዊው ተጫዋች ወኪል የሆነው ካሪም ዱይስ የሁለት ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው ተጫዋች ወደሊግ 1 ክለብ መዛወር በሚችልበት ሁናታ ላይ ለመነጋገር ከፒኤስጂው የስፖርት ጉዳዮች ኃላፊ ጋር መገናኘቱም ተዘግቧል።

ሳላህ ከሩሲያው ዓለም ዋንጫ በኋላ ሊቨርፑልን ሊለቅ ይችላል

እንደስፔኑ ጋዜጣ ዶን ባሎን ዘገባ ከሆነ ሊቨርፑል የአማካኝ ክፍሉን የማያጠናክር ከሆነ ሞሐመድ ሳላህ በዚህ ክረምት ሊቨርፑልን ሊለቅ ይችላል።

ግብፃዊው ተጫዋች ያለውን ምኞት ለክለቡ የገለፀ ሲሆን፣ ሊቨርፑሎች በአማካኝ ክፍላቸው ላይ ያላቸውን አማራጭ ለማስፈት ፈቃደኛ የማይሆኑ ከሆነ ተጫዋቹ በአንፊልድ አይቆይም።

ፈኪር በሊቨርፑል የሚለበሰውን የመለያ ቁጥር መርጦ ነበር

የሊዮኑ ናቢል ፈኪር ወደፕሪሚየር ሊጉ የሚያደርገው ዝውውር ከመሰናከሉ በፊት በሊቨርፑል ለብሶት የሚጫወተውን ቁጥር መርጦ እንደነበር የጎል ድረገፅ ዘገባ አመልክቷል።

ቀዮቹ ተጫዋቹን እንደሚያስፈርሙት እርግጠኛ የነበሩ በመሆናቸው ፈረንሳያዊው ተጫዋች በ2018-19 የውድድር ዘመን ለብሶት የሚጫወተውን የመለያ ቁጥር መርጠው ነበር።

ነገር ግን በመርሲሳይዱ ክለብ እና በፈረናሳዩ ክለብ መካከል የተደረገው ንግግር ባለመሳካቱ ስምምነቱ ሊፈርስ ችሏል።

ፈረንሳይ


የግሪዝማን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከዓለም ዋንጫው በፊት ውሳኔ ሊያገኝ ይችላል

የአንቱዋን ግሪዝማን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከሩሲያው ዓለም ዋንጫ ውድድር በፊት ውሳኔ ሊያገኝ እንደሚችል የቬሪየስ ዘገባ አመልክቷል።

የባርሴሎና የዝውውር ዒላማ የሆነው ግሪዝማን ፈረንሳይ ከአሜሪካን ጋር 1ለ1 ከተለያየችበት የወዳጅነት ጨዋታ በኋላ እንደተናገረው “[ለዓለም ዋንጫው] ገና አንድ ሳምንት ይቀራል። በዚህ ሳምንት ስለወደፊት ዕጣ ፈንታዬ የምናውቅ ይመስለኛል።” ሲል ገልፅዋል።

ታባስ ሮናልዶና ግሪዝማን ባሉበት እንደሚቆዩ እምነት አላቸው

የላ ሊጋው ፕሬዝዳንት ኻቪየር ታባስ ክርስቲያኖ ሮናልዶና አንቱዋን ግሪዝማን እንደቅደም ተከተላቸው በሪያል ማድሪድና በአትሌቲኮ ማድሪድ ይቆያሉ ብለው እንደሚያምኑ የጎል ድረገፅ ዘገባ አመልክቷል።

ሮናልዶ ባለፈው ወር ተከታታይ ሶስተኛ የሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ድሉን ካሳካ በኋላ በክለቡ የሚኖረው ቀጣይ ቆይታ በጥርጠሬ ላይ ወድቋል።

በተመሳሳዩ ባርሴሎና ፍላጎቱን እያሳየ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ምንም እንኳ ግሪዝማን በላ ሊጋው ክለብ እንደሚቆይ ቢናገርም በአትሌቲኮ ማድሪድ የሚኖረው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ግን እርግጥ አይደለም።

“ክርስቲያኖ በሪያል ማድሪድ እና አንቱዋን ግሪዝማን በአትሌቲኮ ማድሪድ ይቆያሉ ብዬ አስባለሁ።” ሲሉ ታባስ ለስፔኑ ሬድዮ ጣቢያ ኦንዳ ሴሮ ተናግረዋል።

ጉቲ የማድሪድን የአሰልጠኝነት ስራ ሊረከብ ነው – ሮናልዶንም የሚሸጥ ይሆናል

እንደዲያሪዮ ጎል ዘገባ ከሆነ ሪያል ማድሪድ ጉቲን አዲስ አሰልጣኙ አድርጎ ለመቅጠር ተዘጋጅቷል። የቀድሞው አማካኝ ሮናልዶን መሸጥን ጨምሮ የቡድን ስብስቡን በሙሉ የመቆጣጠር ዕቅድም አለው።

ማድሪድ በከፍተኛ የዝውውር ዋጋ ኮንትራት ማውሪሲዮ ፓቸቲኖን እና የርገን ክሎፕን ጨምሮ ጉቲን በዋና የአሰልጠኝነት ዕጩ ዝርዝሩ ላይ አስፍሮታል።

እናም ጉቲ የማድሪድ አሰልጣኝነት ሚናን ሲረከብ የበርናባው የመጨረሻ ቆይታው እንደሆነ ያለውን ስሜቱን የገለፀውን ሮናልዶን ከክለቡ የሚቀንስ ይሆናል። በተመሳሳዩ አራት ተጫዋቾችም ክለቡን እንዲለቁ ፈቃድ ያገኛሉ።

ሪያል ማድሪድ ጋርዝ ቤልን ከ222 ሚ.ዩሮ በታች አይሸጠውም

ሪያል ማድሪድ ጋርዝ ቤልን ከ22 ሚ.ዩሮ በታች አይሸጠውም። ይህ ደግሞ ኔይማር ፒኤስጂን የተቀላቀለበት የዝውውር ዋጋ ነው።

በኮንትራቱ ላይ 877 ሚ.ፓውንድ የውል ማፍረሻ ስምምነት ያለው እና በወኪሉ በኩል በበርናባው ስለሚኖረው የወደፊት ዕጣ ፈንታ እየተነጋገር የሚገኘው ቤል የማንችስተር ዩናይትድ የዝውውር ዒለማ ሆኖ ይገኛል። ይሁን እንጂ ቤል ማድሪድን ሊለቅ የሚችለው ኔይማር ወደበርናባው የሚዛወር ከሆነ ብቻ እንደሆነ የዘገበው ኤቢስ ስፖርት ነው።

ማርሴሎ ኔይማር ለሪያል ማድሪድ መፈረም የማይችልበት ምክኒያት እንደሌለ ገለፀ

የሪያል ማድሪዱ ተከላካይ ማርሴሎ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በበርናባው ቆየም አልቆየ ኔይማር በዚህ ክረምት ክለቡን ለመቀላቀል የማይችልበት ምክኒያት እንደሌለ መግለፁን የስፔኑ ጋዜጣ አስ ዘገባ አመልክቷል።

የብራዚል ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቹ በዓለም ዋንጫ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገረው “ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሪያል ማድሪድ ኃላፊ አይደለም። እናም ክርስቲያኖ አዚያ በመኖሩ ኔይማር ለምን አይቀላቀለንም? ለኔይማር የሪያል ማድሪድ በር ክፍት ነው። ማድሪድ ሁልጊዜም የሚመለከተው ምርጥ ተጫዋቾችን ነው። አንድ ቀን ኔይማር በሪያል ማድሪድ ይጫወታል።” ሲል ገልፅዋል።

ሳልህ ለራሞስ “እሺ” የሚልስ እንዳልሰጠው ገለፀ

ሞሐመድ ሳላህ በሻምፒዮንስ ሊጉ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ስለመውደቁ ጉዳይ ከራሞስ ጋር መነጋገሩን ገልፃ ነገር ግን “እሱ [ሰርጂዮ ራሞስ] የፅሁፍ መልዕክት ልኮልኛል። ነገር ግን ፈፅሞ “እሺ” ሚል መልስ አልሰጠሁትም።” ሲል መናገሩን የማርካ ዘገባ አመልክቷል።

በደልፊዩ ዝውውር ባርሳና ዋትፎርድ ከስምምነት ላይ ደረሱ

በጄራድ ደልፊዩ የዝውውር ጉዳይ ላይ ባርሳሎና እና ዋትፎርድ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን የስፔኑ ስፖርት ጋዜጣ ዘገቧል።

ሆርኔቶቹ ስፔናዊውን የፊት ተጫዋች በቀጣዩ ሳምንት በ13 ሚ.ፓውንድ የሚያስፈርሙትም ይሆናል።

ባርሴሎና ከደዮንግ ወኪል ጋር ሊነጋገር ነው

እንደአስ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ባርሴሎና በዚህ ሳምንት የፍራንኪ ደ ዬንግ ዝውውርን ፈር ለማስያዝ ከተጫዋቹ ወኪል ጋር በዚህ ሳምንት በጠረጴዛ ዙሪያ ይነጋገራል።

ባርሳ የ23 ዓመቱን የአያክስ አማካኝ ለማስፈረም ከ30-35 ሚ.ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ዋጋ ወጪ እንደሚያደርግም ተዘግቧል።

ፔፕ ጋርዲዮላ ባርሳን ፈፅሞ ዳግመኛ እንደማያሰለጥን ተናገረ

ፔፕ ጋርዲዮላ በርሴሎናን ፈፅሞ ዳግመኛ እንደማያሰለጥን ለስፔኑ ቲቪ3 ተናግሯል።

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ በኑ ካም ሶስት የላ ሊጋ እና ሁለት የሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ክብሮችን ጨምሮ 14 ዋንጫዎችን ማንሳት የቻለባቸው ሶስት ስኬታማ ዓመታትን አሳልፏል።

ጣሊያን


ሃምሲክ ወደቻይና ሊያመራ ይችላል

እንደጣሊያኑ ኮሪየር ዴሎ ስፖርት ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ስሎቫኪያዊው ኮከብ ማሬክ ሃምሲክ ወደቻይና ሊያመራ ይችላል።

በናፓሊ እና በፋቢዮ ከናቫሮ የሚሰለጥነው የቻይናው ክለብ ጉዋንዡ ኤቨርግራንዴ መካከል የተደረገው ውይይት በስምምነት መጠናቀቁ ተዘግቧል።

ቼልሲ የፍሎሬንዜ ፈላጊ ሆኗል

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ምንም እንኳ ምንም አይነት ተጨባጭ ጥያቄ ባያቀርብም የሮማውን ተከላካይ አሌሰንድሮ ፍሎሬንዜን ለማስፈረም መፈለጉን ግን ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት ዘግቧል።

ሊችስቴነር አርሰናል የቀድሞ ክለቡን እንደሚያስታወሰው ገለፀ

አዲሱ የአርሰናል ፈራሚ ስቴፋን ሊችስቴነር አርሰናል የቀድሞ ክለቡን እንደሚያስታወስው ገልፅዋል።

ተጫዋቹ “አርሰናል አስደናቂ የስራ ዕቅድ ያለው ታላቅ ክለብ ነው።” ሲል ለስካይ ኢታልያ ተናግሮ “ይህም ዓለማችን ወደሻምፒዮን ሊጉ መመለስ ወደነበረው ከሰባት ዓመት በፊት የነበረውን ጁቬንቱስንም ያስታወሰኛል።” ሲል ጨምሮ ገልፅዋል።

ጀርመን


ማሪዮ ገትዘ የቀድሞ አሰልጠኞቹን (ባለፈው ዓመት በዶርትሙንድ ያሰለጠኑትን ፒተር ስቶገርን እና በባየር ሙኒክ ቆይታው የባየር አሰልጣኝ የነበሩትን ፔፕ ጋርዲዮላን) “የሰውን ችግር እንደራስ ማየት የሚቸግራቸው” በማለት መተቸቱን የጀርመኑ የዳዝን ኦንላየን ስትሪሚንግ ሚዲያ ዘገባ አመልክቷል።

Advertisements