“ማድሪድን የለቀኩት የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድንን ለማሰልጠን አይደለም”- ዚዳን

ከሪያል ማድሪድ ጋር ሳይታሰብ በቅርቡ የተለያየው ዚነዲን ዚዳን ውሳኔውን የወሰነው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድንን ለማሰልጠን ፈልጎ እንዳልሆነ አሳወቀ።

ሪያል ማድሪድ የቻምፕየንስ ሊጉን ዋንጫ ለሶስተኛ ተከታታይ ጊዜ እንዲያነሳ ያደረገው ዚዳን ክለቡን ለመልቀቅ የወሰነበት ምክንያት አሁንም አነጋጋሪቱ አላቆመም።

አሰልጣኙ ክለቡ አዲስ ለውጥ ያስፈልገዋል በሚል በቀጣይ አመት አሁን ያስመዘገበውን ስኬት ለመድገም እንደሚቸገር በመስጋት ከማድሪድ ጋር ተለያይቷል።

ከቡድኑ ጋር ከተለያየ በኋላ ግን ስሙ ከፈረንሳይ እና ከኳታር ብሔራዊ ቡድን ጋር ተያይዞ ቆይቷል።

በተለይ የ 2022 የአለም ዋንጫ አዘጋጇ ኳታር ዚዳንን ለመቅጠር ከፍተኛ ደሞዝ ማቅረቧ ተሰምቶ ነበር።

አሰልጣኙ ግን ማድሪድን የለቀኩት ፈረንሳይን ለማሰልጠን ብሎ እንዳልሆነ ተናግሯል።

“ማድሪድን የለቀኩት ፈረንሳይን ለማሰልጠን አይደለም አሁን በጣም አስፈላጊው ነገር የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድንን መደገፍ ነው።እኔ ቡድኑን እደግፋለው።ለሁለተኛ ጊዜ የአለም ዋንጫ ማሸነፍ እንፈልጋለን።

አሰልጣኙ ጨምሮ ስለወደፊት ስራው ውሳኔ ላይ አለመድረሱን ተናግሯል።

Advertisements