ኪሊያን ምባፔ ልምምድ ላይ ተጎዳ

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የአጥቂ መስመር ተሰላፊው ኪሊያን ምባፔ ዛሬ ልምምድ ላይ ጉዳት ካጋጠመው በኋላ በአለም ዋንጫው ላይ መሳተፉ አጠራጣሪ ሆኗል።

ወጣቱ ተጫዋች በዲድየር ዴሾ የቡድን ስብስብ ውስጥ ከተካተቱት ኮከቦች ውስጥ ይገኝበታል።

ተጫዋቹ የአለም ዋንጫው ሊጀመር ሁለት ቀናት ብቻ ሲቀሩት ዛሬ ልምምድ ላይ እያለ ጉዳት አጋጥሞታል።

ለጉዳት የዳረገው ደግሞ ሌላው የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋች የሆነው አዴል ሬሚ ሲሆን ምባፔም ከጉዳቱ በኋላ መሬት ላይ ወድቆ ታይቷል።

ቁርጭምጭሚቱ ላይ ጉዳት እንዳጋጠመው የተነገረው ምባፔ ህክምና ከተደረገለት በኋላ ልምምዱን አቋርጦ ወደ መልበሻ ቤት አቅንቷል።

የጉዳቱ መጠን ባይታወቅም የአለም ዋንጫው ከመቃረቡ አንፃር ለታላቀየ ውድድር መድረሱ አጠራጣሪ ሆኗል።

ቡድኑ የተጫዋቹ የጉዳት ሁኔታን ከምርመራ በኋላ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

Advertisements