2006 ጀርመን – በአንድ ጨዋታ ሶስት ቢጫ ካርድ

በአንድ ጨዋታ ላይ ሶስት ቢጫ ካርዶች የታዩበት አወዛጋቢው ጨዋታ በ 2006ቱ የጀርመን የአለም ዋንጫ ላይ ከማይዘነጉ የዳኝነት ስህተቶች ውስጥ አንዱ ነበር።

በ2006 የአለም ዋንጫ ላይ እንግሊዝን የወከሉት ብቸኛ ዳኛ ግርሀም ፖል ነበሩ።

እኝህ የተከበሩ እንግሊዛዊው ዳኛ በ 2006 የአለም ዋንጫ ላይ የሰሩት ስህተት እስከአሁን ድረስ በአስገራሚነቱ ይነሳል።

በምድብ ስድስት አውስትራሊያ ከክሮሺያ ጋር ያደረጉትን የምድባቸው ጨዋታ ሲሙኒች የተባለውን የክሮሺያ ተጫዋች ሶስት ጊዜ ቢጫ አሳይተውታል።

ግርሀም ፖል ቀደም ብለው ለተጫዋቹ ያሳዩት ቢጫ ካርድ በማስታወሻቸው ላይ የተሳሳተ ቁጥር እና ስም በመመዝገባቸው ሲሙኒችን ቀይ ካርድ ለመስጠት ሶስት ቢጫ ካርድ አስፈልጓቸዋል።

በወቅቱ ከምድብ ጨዋታዎች ባለፈ ታላላቅ የጥሎማለፍ ጨዋታዎችን ያጫውታሉ ተብሎ ታስቦ የነበሩት እኝህ ዳኛ በሰሩት ጥፋት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

እሚገርመው ግን በዚህ ጨዋታ ላይ ግርሀም ፖል ሲሳሳቱ ረዳት ዳኞቹ እና አራተኛው ዳኛ ዝም ማለታቸው ነው።

ግርሀም ፖልም ስህተታቸውን ለመቀበል በመልበሻ ቤት ጨዋታውን በመልሶ እይታ መመልከት አስፈልጓቸው ነበር።

እንግሊዞች በዘንድሮው የአለም ዋንጫ ላይም አንድም ዳኛ እንዳላስመረጡ ይታወቃል።

Advertisements