ሞ ሳላህ በዛሬው ጨዋታ የመሰለፍ እድሉ ምን ያህል ነው? አሰልጣኙ ሄክቶር ኩፐር ምላሽ አላቸው

የግብፅ ብሔራዉ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት ሄክቶር ኩፐር ዛሬ ከሰአት ኡራጋይን በሚገጥመው ቡድናቸው ውስጥ የ ሞ ሳላህ የመሰለፍ እድሉን አስመልክቶ በመግለጫቸው ተናግረዋል። 

አፍሪካዊቷ ግብፅ በምድብ አንድ የመጀመሪያዋን ጨዋታ ከላቲን አሜሪካዋ ጠንካራ ሀገር ኡራጋይ ጋር ዛሬ ታደርጋለች።

የምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታ በመክፈቻ እለት ራሺያ ሳውዲአረቢያ ላይ 5 ጎል በማስቆጠር አሸንፋለች።

ዛሬ ከሰአት ደግሞ የፈርኦኖቹ እና የኡራጋይ ጨዋታ በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቅ ሲሆን ከጨዋታው በፊትም መግለጫ የሰጡት ሄክቶር ኩፐር ስለ ሞ ሳላህ የመሰለፍ እድል መልካም ዜና ተናግረዋል።

አሰልጣኙ ሳላህ “100% ሊያስብል በሚችል ለጨዋታው ዝግጁ ነው።”በማለት አረጋግጠዋል።

ተጨዋቹም ሰሞኑን በማህበራዊ ገፁ ላይ የመጫወቻ ጫማውን ይዞ “ይህን ጫማ የማደርገው ለ100 ሚሊየን የግብፅ ህዝብ ነው።” በማለት ለፍልሚያው እንደተዘጋጀ መናገሩ ይታወሳል።

ይህ ደግሞ ከ28 አመታት በኋላ የመጀመሪያዋን የአለም ዋንጫ ጨዋታ ለምታደርገው ግብፅ ትልቅ ዜና ነው ማለት ይቻላል።

ሳላህ በሊቨርፑል የመጀመሪያ አመት ቆይታው ድንቅ እንቅስቃሴ በማድረግ በሁሉም ውድድሮች 44 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ተጫዋቹ በአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ጉዳት ካጋጠመው በኋላ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ልምምድ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወሳል።

Advertisements