ሹመት – የቀድሞ የፕሪምየር ሊጉ ጠንካራ ቡድን ማርሴሎ ቤልሳን በአሰልጣኝነት ቀጠረ

አርጀንቲናዊው የቀድሞ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን እና የስፔኑ ቢልባኦ አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ የአንድ እንግሊዝ ቡድን አሰልጣኝ ሆነዋል።

ቤልሳ በብሔራዊ ቡድን ቺሊኒም ይዘው የነበረ ሲሆን የፈረንሳዩ ማርሴን የማሰልጠን እድልም አግኝተው ነበር።

በተለይ በአትሌቲክ ቢልባኦ ቆይታቸው ቡድኑ ለዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ እንዲሁም በኮፓ ዴልሬ የፍፃሜ ጨዋታ ማብቃት ችለው ነበር።

የ 62 አመቱ አሰልጣኝ አሁን ደግሞ ወደ እንግሊዝ በማቅናት የሊድስ ዩናይትድ አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።

አሰልጣኙ በኢላንድ ሮድ ሊራዘም የሚችል የሁለት አመት የሚያቆያቸው ኮንትራት ፈርመዋል።

“የሊድስ ዩናይትድ አሰልጣኝ ለመሆን ጥያቄውን በመቀበሌ ደስተኛ ነኝ።ሁልጊዜ በእንግሊዝ የመስራት ፍላጎት ነበረኝ።በእግርኳስ ህይወቴ በእንግሊዝ ለመስራት የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበውልኛል፣ ነገርግን ትክክለኛው ፕሮጀክት ያለው ቡድን እስካገኝ የተቀበልኩት ቡድን አልነበረም።

“ነገርግን እንደ ሊድስ ዩናይትድ አይነት ታሪክ ያለው ቡድን ጥያቄ ሲያቀርብልኝ እምቢ ማለት አልቻልኩም።” በማለት ቤልሳ ተናግረዋል።