የዓለም ዋንጫ፡ ፖርቱጋል ከ ከስፔን፣ የኃያላኑ ፍልሚያ ቅድመ ዳሰሳ

ይህ ሁለቱ ኃያላን ብሄራዊ ቡድኖች በሩሲያው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የሚያደርጉት የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸው ነው።

ምንም እንኳ ሁለቱ ጎረቤት ሃገሮች ረጅም ጊዜ የዘለቀ ተቀናቃኝነት ቢኖራቸውም ይህ ጨዋታ ስፔናውያኑ 1ለ0 ማሸነፍ ከቻሉበት የደቡብ አፍሪካው የ16ቱ ዙር ጨዋታ ወዲህ በትልቅ ውድድር ሲገናኙ ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ ነው።

ጨዋታ፡ ፓርቱጋል ከ ስፔን
ቀን፡ ሰኔ 8፣ 2010 ዓ.ም
ሰዓት፡ ምሽት 3 (በኢትዮጵያ አቆጠጠር)
ሜዳ፡ ፊሽት ኦሎምፒክ ስታዲየም

በአጠቃላይ ሁለቱ ሃገራት በ35 አጋጠሚዎች ላይ እርስበርስ ተገናኝተው ስፔን በ16 ጨዋታ ላይ በመርታት ስትመራ ፓርቱጋል ማሸነፍ የቻለችው ግን በስድስቱ ላይ ብቻ ነበር። ከዚህ የሩሲያው ውድድር በፊት ሚዛኑን የጠበቀ የወጣት እና አንጋፋ ተጫዋቾች ውህደት ያለውን ቡድን የገነቡት ላ ሮኻዎቹ (ስፔኖች) በተወሰነ መልኩም ቢሆን የስነልቡና የበላይነታቸው ሳይወሰደባቸው እንደማይቀር ይጠበቃል። ነገር ግን በውድድሩ ዋዜማ የአሰልጣኝ ለውጥ የማድረግ ውሳኔ ማሳለፋቸው የሚፈጥርባቸው የተፅዕኖ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ግልፅ አይደለም።

በሌላ በኩል የዓለም ኮከቡን የያዙት የአውሮፓ ሻምፒዮኖቹ በውድድሩ ላይ ከምንጊዜውም በላይ አንዳች የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ቁርጠኛ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

አሰልጣኞችና ተጫዋቾች ስለጨዋታው ምን አሉ?

ጆአ ሞቲንሆ (ፓርቱጋል)

“ፓርቱጋል ዋንጫውን ወደሃገራቸው ይዘው እንደሚሄዱ ከታጩ ቡድኖች መካከል አንዷ ናት። ሌሎች ቡድኖችም ከዚህ ቀደም ባሳኩት ነገር እንደሚያሸንፉ ማሰብ የሚገርም አይደለም። እኛ የአውሮፓ ሻምፒዮን ነን። ነገር ግን ያ ዋንጫውን እንድናሸንፍ አያደርገንም።

“ያለን ወጣትና ትኩረት ያረፈበት እንዲሁም ከፍ ያለ ነገር የሚያልም ቡድን ነው ያለን።”

ፈርናንዶ ሄሮ (ስፔን):

“ግባችን ለዓለም ዋንጫው ክብር መብቃት ነው። [ለተጫዋቾ] የነገርኳቸውም ይህንኑ ነው። ይህ [የአሰልጣኝ ለውጥ] የይቅራት ምክኒያት አይሆንም።

“ከፊታችን የሚደንቅ ፍልሚያ እንደሚጠብቀን ለተጫዋቾቹ ነግሬያቸዋለሁ። እናም ህልማችንን ከሚያሳካልን ነገር ውጪ ምንም ልናስብ አንችልም።”

ግምታዊ አሰላልፎች

ፓርቱጋል: ሩይ ፓትሪሲዮ፣ ራፋኤል ጎሬሮ፣ ጆሴ ፎንቴ፣ ፔፔ ሴድሪች፣ ጆአ ማሪዮ፣ ዊሊያም፣ በርናርዶ ሲልቫ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ጎናካሎ ጉዴስ

ስፔን: ዴቪድ ደ ኽያ፣ ጆርዲ አልባ፣ ሰርጂዮ ራሞስ፣ ጄራርድ ፒኬ፣ ናቾ፣ ሰርጂዮ ቡስኬት፣ ቲያጎ አልካንትራ፣ አንድሬስ ኢንየስታ፣ ኢስኮ፣ ዳቪድ ሲልቫ፣ ዲያጎ ኮስታ

ይህን ያውቃሉ?

የሁለቱ ቡድኖች ፍልሚያ ኃይለኛ ተቀናቃኝነት ያለው እንደመሆኑ ስፔን ከፓርቱጋል ጋር ባደረገችው ጨዋታ ከሜዳ በቀይ ካርድ በሚሰናበት ተጫዋች አንፃር ያላት ቁጥራዊ መረጃ ከፓርቱጋል ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ ነው። ምክኒያቱም ላሮ ሮሃዎቹ በዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ በአስር ተጫዋቾች ጨዋታ ለመጨረስ የተገደዱት አንድ ጊዜ ብቻ ነው። እሱም በ1994 ከኮሪያ ሪፐብሊክ ጋር 2ለ2 በተለያዩበት ጨዋታ የቴኒስ ሻምፒዮኑ ራፋኤል ናዳል አጎት የሆነው ሚጉኤል አንገል ናዳል በ25ኛው ደቂቃ የተሰናበተበት ጨዋታ ነበር።

Advertisements