ዴቪድ ዲሂያ እና ማን ዩናይትድ ለተጨማሪ አመታት ሊወዳጁ ነው


በየዝውውር መስኮቱ ስሙ ከማድሪድ ጋር የሚያያዘው ዴቪድ ዴሂያ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የሚያቆየውን የአምስት አመት ኮንትራት ለመፈረም ጫፍ ላይ ይገኛል።

ስፔናዊው ግብ ጠባቂ በፕሪምየርሊጉ ካሉ ግብጠባቂዎች ውስጥ ኮከብ መሆኑ ባለፉት ሶስት የውድድር አመታት አስመስክሯል።

ላይም ሪያል ማድሪድ ተጫዋቹን ለማስፈረም እጅግ ቢቃረብም ዝውውሩ በመጨረሻ ባለመሳካቱ ዲሂያ ለአምስት አመታት ኮንትራቱን ማራዘሙ ይታወሳል።

እንደ ኢንዲፐንደንት ጋዜጣ መረጃ መሰረትም ዩናይትድ ተጫዋቹን ለሌላ አምስት አመታት ለማስፈረም መቀረቡን አሳውቋል።

ይህ ከሆነ ደግሞ ዴሂያ እድሜው 32 እስኪሆነው ድረስ የቀዮቹ ግብ ጠባቂ ሆኖ የሚቆይ ይሆናል።

በአዲሱ ስምምነቱም ከፍተኛ የሆነ ሳምንታዊ ደሞዝ እንደሚያገኝ የሚጠበቅ ሲሆን በክለቡም የማይክል ካሪክ ምትክ በመሆን አምበል እንደሚሆን ይጠበቃል።

በተከፈተው የዝውውር መስኮትም ሪያል ማድሪድ ተጫዋቹን የማስፈረም ፍላጎት ቢኖረውም እስከ 100 ሚሊየን ፓውንድ የሚያስወጣው በመሆኑ ትኩረቱን ወደ ሮማው ግብጠባቂ አሊሰን ላይ ማድረጉ ታውቋል።