ሩሲያ 2018 -ክርስቲያኖ ሮናልዶ የነ ፔሌን ሪከርድ ተጋራ

በ 2018 የአለም ዋንጫ የመጀመሪያውን ጨዋታ ሀትሪክ መስራት የቻለው ሮናልዶ እነ ፔሌ ይዘውት የነበረውን ሪከርድ ተጋራ።

ምሽት ላይ ስፔን ከ ፖርቹጋል ያደረጉት የአለም ዋንጫው ተጠባቂው ጨዋታ ሳይሸናነፉ 3-3 ተለያይተዋል።

በጨዋታው ሮናልዶ በዴቪድ ዴሂያ መረብ ላይ ሶስት የተለያዩ አይነት ጎሎችን አስቆጥሮበታል።

በጨዋታው ሮናልዶ መጀመሪያ ላይ በፍፁም ቅጣት ምት እንዲሁም ከእረፍት በፊት በጨዋታ እንቅስቃሴ፣የመጨረሻዋን ደግሞ በቅጣት ምት አስቆጥሯል።

ተጫዋቹ የመጀመሪያ የአለም ዋንጫ ከተሳተፈበት 2006 ጀምሮ በተካሄዱት አራት የአለም ዋንጫዎች በሙሉ ጎል አስቆጥሯል።

ይህ ደግሞ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ በአራት የአለም ዋንጫዎች ላይ ጎል ያስቆጠሩት እነ ፔሌ፣ሚሮስላቭ ክሎስ፣ኡዌ ሲለር ጋር እንዲስተካከል አድርጎታል።

ተጫዋቹ እድሜው 33 ቢደርስም እስከ ሰላሳዎቹ መጨረሻ እደሚጫወት በቅርቡ መናገሩ ተከትሎ በ 2022 የሚደረገው የአለም ዋንጫ ላይ ሊሳተፍ ይችላል።

2022 ላይ በኳታር በሚደረገው የአለም ዋንጫ ላይ ጎል ማስቆጠር የሚችል ከሆነ ደግሞ በአምስት የአለም ዋንጫ ላይ ጎል በማስቆጠር ብቸኛው ተጫዋች ይሆናል።

Advertisements