ዓለም ዋንጫ | ፈረንሳይ ከ አውስትራሊያ፣ የምድብ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

በምድብ ሐ ላይ የሚገኙት የፈረንሳይ እና አውስትራሊያ ዛሬ (ቅዳሜ) እኩለ ቀን ላይ የውድድሩን እና የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የዲዲየ ደሾው ሰማያዊዎቹ ዋንጫውን እንደሚያነሱ ከፍተኛ ግምት ከtpሰጣቸው ብሄራዊ ቡድኖች መካከል አንዱ ቢሆንም በ1998 ዋንጫውን ካነሱ በኋላ በተሳተፉበት የ2002 እና 2010 ከዓለም ዋንጫው ከምድብ ማጣሪያ ውጪ የሆኑበት ጊዜም አይዘነጋም።

አውስትራሊያ በአጠቃይ መሳተፍ ከቻለችበት አምስት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ይህ በተከታታይ የምትሳተፍበት አራተኛው ውድድሯ ሲሆን፣ በቀጣይ ከምታደርጋቸው ሶስት የምድብ ጨዋታዎች መልካም ውጤት የማስመዝገብ ተስፋም ሰንቃለች።

ምድብ ሐ ተጫ ድል አቻ ሽን ነጥብ
ፈረንሳይ 0 0 0 0 0 0 0
አውስትራሊያ 0 0 0 0 0 0 0
ፔሩ 0 0 0 0 0 0 0
ዴንማርክ 0 0 0 0 0 0 0

መቼ ይደረጋል?

ፈረንሳይ ከ አውስትራሊያ በካዛን አሬና የሚያደርጉት ጨዋታ ቅዳሜ ሰኔ 9፣ 2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጠጠር እኩለ ቀን 7፡00 ሰዓት ላይ የሚደረግ ነው።

የሁለቱ ሃገራት የእርስ በእርስ ግንኙነት

ፈረንሳይ እና አውስትራሊያ በድምሩ አራት ጊዜ እርስበእርስ ተገናኝተው ተጫውተዋል። በቅርብ ጊዜ ያደረጉት ጨዋታ በ2013 ሲሆን በጨዋታው ፈረንሳይ አውስትራሊያን ሁለት ጊዜ ካሸነፈችበት ጨዋታ አንዱ በሆነው ጨዋታ 6ለ0 ማሸነፍ ችላለች። አውስትራሊያ ፈረንሳይን ያሸነፈችበት ብቸኛ ጨዋታ በ2001 የኮንፌሬዴርሽን ዋንጫ ጨዋታ ነበር። ከአምስት ወራት በኋላ ባደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ ደግሞ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የቡድን ዜና

ፈረንሳዮች በገዛ ሃገራቸው በ2016 ፍፃሜ በፓርቱጋል የደረሰባቸውን ሽንፈት ወደኋላ ትተው ለ2018 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ማለፍ ችለዋል።

ሰማያዊዎቹ ከአራት ዓመት ባፊት በብራዚሉ የዓለም ዋንጫን የጀመሩት ሆንዱራስን 3ለ0 በማሸነፍ ነበር። ዲዲ ደሾ በዚህ የካዛኑ ጨዋታ ግብ ማስቆጠር አቅም ያላቸው በርካታ አማራጭ አጥቂዎች ያሏቸው ቢሆንም፣ ከኮከቡ አንቱዋን ግሪዝማን እና ከወጣቱ ድንቅ ተጫዋች ኪሊያን ምባፔ ጋር ማንን ያጣምራሉ? የሚለው ራስ ምታት ሳይሆንባቸው እንደማይቀር ይጠበቃል።

ሶከረሶቹ (አውስትራሊያውያኑ) በቀደሙት ዓለም ዋንጫዎች ላይ አምስት ግቦችን ማቆጠር በቻለው አንጋፋው ተጫዋቻቸው ቲም ካሂል ግቦች ታግዘው የደርሶ መልስ ማጣሪያቸውን በሚገባ ተወጥተው ለዚህ ዓለም ዋንጫ በቅተዋል። ካሂል 38 ዓመት ዓመት የሞለው ዕድሜው ገደብ እስካልፈጠረበት ድረስ በአራት የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታዎች ላይ በማስቆጠር ከአንጋፋዎቹ ፔሌ፣ ኡዌ ሲለር እና ሚሮስላቭ ክሎዘ ተርታ ሊመደብም ይችላል።

የተረጋገጡ አሰላለፎች

ፈረንሳይ (4-3-3):
ሎሪስ | ኸርናንዴዝ፣ ኡምቲቲ፣ ቫራን፣ ፓቫርድ፣ ፓግባ፣ ካንቴ፣ ቶሊሶ፣ ዴምቤሌ፣ ግሪዝማን፣ ምባፔ

ተቀያሪያዎች፡ ክምፔምቤ፣ ለማር፣ ዥሩ፣ ማቲዩዲ፣ ንዞንዚ፣ ማንዳንዳ፣ ራሚ፣ ፈኪር፣ ሲዲቤ፣ ቱዋቪን፣ ሜንዲ፣ ኦውሬሎ

አውስትራሊያ(4-4-2):
ሪያን | በሂች፣ ሴንስበሪ፣ ሪስዶን፣ ክሩዝ፣ ሙይ፣ ጄዲናክ፣ ሌኪ| ረጊች፣ ናቦት

ተቀያሪዎች፡ ዳግኔክ፣ ሜሬዲር፣ ካሂል፣ ጁርማን፣ ሉዎንጎ፣ ጁሪች፣ ጆንስ፣ ማክላረን፣ አርዛኒ፣ ቩኮቪች፣ ፔትራቶስ፣ ኢርቪን

ይህን ያውቃሉ?

ቫን ማርዊክ ሳኡዲ አረቢያን ለ2018 የሩሲያው ዓለም ዋንጫ ማብቃት ቢችሉም ከአረጓዴ ፋልከኖቹ ጋር የኮንትራት ማራዘሚያ ስምምነት ለማድረግ ሳይችሉ ቀርተው አንጌ ፓስቴኮግሉን ተክተው የአውስትራሊያ አሰልጣኝ ሆነዋል። የ66 ዓመቱ ሰው ሶከሩሶቹን በ2006 እስከ16ቱ ዙር ድረስ ማብቃት ከቻሉት ጉህ ሂድኒክና በ2010 የደቡብ አፍሪካው ዓለም ዋንጫ አሰልጣኝ ከነበሩት ፒም ቬርቢክ ቀጥለው አስትራሊያን ማሰልጠን የቻሉ ሶተኛው ሆላንዳዊ አሰልጣኝ ናቸው።