የሩሲያ የአለም ዋንጫ በቁጥር

ባለፈው ሀሙስ በሩሲያ የተጀመረው 21ኛው የሩሲያ የአለም ዋንጫ ቁጥራዊ መረጃዎች ቀርበዋል።

186 ☞ በ 2014 የብራዚል የአለም ዋንጫ የተሳተፉ እንዲሁም በ 2018 የሩሲያ የአለም ዋንጫ በድጋሚ ተሳታፉ የተጫዋቾች ብዛት 186 ነው።

11 ☞ ምንም እንኳን ጣሊያን በአለም ዋንጫው ባትሳተፍም የጁቬንቱስ 11 ተጫዋቾች በአለም ዋንጫው ላይ ተሳትፈዋል።

2.01m ☞ በአለም ዋንጫው ረጅሙ ተጫዋች የክሮሺያው ግብ ጠባቂ ሎቭሬ ካሊኒች የሚረዝመው በሜትር 2.01 ነው።

1.64m ☞ አጭሩ ተጫዋች ደግሞ የሳውዲ አረቢያው የመስመር ተጫዋች የሀያ አልሸሪ ነው።

736 ☞ ከ 311 ክለቦች የተውጣጡ 736 ተጫዋቾች በአለም ዋንጫው ላይ ተሳታፊ ናቸው።

4 ☞ በ 1070ዎቹ የተወለዱ በሩሲያ የአለም ዋንጫ የሚሳተፉ አራት ተጫዋቾች አሉ።እነሱም ኢሳም ኤል ሀድሪ(ግብፅ)፣ራፋኤል ማርኩዌዝ(ሜክሲኮ)፣ሰርጂ ኢግናሼቪች(ራሺያ) እና ቲም ካሂል(አውስትራሊያ) ናቸው።

16 ☞ የጀርመኑ ሚሮስላቭ ክሎስ በአለም ዋንጫ በአጠቃላይ ያስቆጠራቸው 16 ጎሎች በሪከርድነት ተመዝግበዋል።

1 ☞ አይስላንድ እና ፓናማ ለመጀመሪያ ጊዜ በሩሲያው የአለም ዋንጫ ተሳታፊ ናቸው።

16 ☞ ከአንድ ክለብ ብዙ ተጫዋቾች በአለም ዋንጫው የተሳተፉት ከማን ሲቲ ሲሆን ብዛቱ 16 ነው።ማድሪድ እና ባርሴሎና (15) እና (14) አሳትፈዋል።

49 ☞ በአለም ዋንጫው ከሚሳተፈ ውስጥ 49 የሚሆኑ ተጫዋቾች የተወለዱት በፈረንሳይ ነው።

200 000 ☞ በአለም ዋንጫው ተሳታፊ የሆኑ 32 ቡድኖችን ለመደገፍ እስከ 200 ሺ ደጋፊዎች ራሺያ ደርሰዋል።

Advertisements