አለም ዋንጫ 2018 – ሀሪ ኬን ቱኒዚያ ላይ ሀትሪክ ለመስራት ማቀዱን ተናገረ

የክርስቲያኖ ሮናልዶ ሀትሪክ በመጠኑም ቢሆን በሱ ላይ ጫና እንደፈጠረ እና በምሽቱ ጨዋታ ላይ ቱኒዚያ ላይ ሀትሪክ ለመስራት ማቀዱን ሀሪ ኬን ተናግሯል።

የአለም ዋንጫ የ አምስተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ሲካሄዱ እንግሊዝ ከአፍሪካዊቷ ቱኒዚያ ጋር ትጫወታለች።

በወጣቶች የተዋቀረው የጋሪ ሳውዝጌት ቡድን ከምድቡ ለማለፍ እንደማይቸገር ቢነገርም ምሽት ላይ ቱኒዚያን በቀላሉ ትረታለች ተብሎ አይታሰብም።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ስፔን ላይ ሀትሪክ መስራቱ ሌሎች ኮከብ ተጫዋቾች ላይ ጫና እንደፈጠረ እየተነገረ ይገኛል።

ሀሪ ኬንም እሱ ላይ ጫና እንደፈጠረ በማመን ቱኒዚያ ላይ ሀትሪክ ለመስራት ማቀዱን አሳውቋል።

“ባለፉት ጥቂት አመታት እራሴን አሻሽያለው።አሁን ደግሞ ለአለም ያለኝን ለማሳየት እዚህ ተገኝቻለው።

“በእርግጠኝነት ሮናልዶ ሀትሪክ መስራቱ እኔ ላይም ትንሽ ጫና ፈጥሮብኛል።እሱ አስደናቂ በነበረው ጨዋታ ላይ ምርጥ ነበር።ቱኒዚያ ላይ ሀትሪክ ሰርቼ ከሱ ጋር እኩል እንደምሆንም ተስፋ አደርጋለው።”ሲል ኬን ተናግሯል።

Advertisements