ዓለም ዋንጫ | ፓላንድ ከ ሴኔጋል የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

ሴኔጋል በ2002 በመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ተሰትፎዋ በቱርክ በወራቃማው ግብ ከመሸነፏ አስቀድሞ ያለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮኗን ፈረንሳይን በመክፈቻው ጨዋታ ማሸነፍ ችላ ነበር። ያ ቡድንም በሃገሪቱ እግርኳስ ላይ ታሪክ መፃፍ ችሏል። የሊቨርፑሉን ሳዲዮ ማኔን ያቀፈው ይህ አዲሱ የሴኔጋል ትውልድም በአህጉሪቱ

ታሪክ ላይ ሌላ ተጨማሪ ታሪክ ለማከል ዝግጅቱን አጠናቆ ሩሲያ ከትሟል።

የታራንጋ አምበሶቹ በ2016 የአውሮፓ ዋንጫ ከሩብ ፍፃሜ በአሳዛኝ ሁኔታ በመለያ ምት ተሸንፎ የወጣው የፓላንድ ቡድን ላይ ኃያል ጥፍራቸውን ለማሳረፍ ተዘጋጅተዋል።

የአዳም ንዋልከዋው ቡድን ከ12 ዓመታት ከውድድሩ የለመሳተፍ ጉዞ በኋላ በዚህ ጨዋታ ትኩረቱን በሙሉ በማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ 16 ግቦችን ከመረብ ላይ ባሳረፈው ሮበርት ሊቫንዶውስኪ ላይ እንደሚያሳርፍም ይጠበቃል። የባየር ሙኒኩ አምበልም በስፓርታክ ስታዲየም የሚደርገውን የዓለም ዋንጫ ተልዕኮውን ከፍ ባለ ብቃት እንደሚወጣ ይጠበቃል።

ግምታዊ አሰላለፎች

ፓላንድ: ዎሺክ ሼዝኒ፣ ማሼጅ ሪበስ፣ ሚቻል ፓዝዳን፣ ያን ቤድናሬክ፣ ሉከዝ ፒሼክ፣ ካሚል ግሮሲኪ፣ ጃሴክ ጎራልስኪ፣ ግርዝጎራዝ ክርቾዊያክ፣ ጃኩብ ብላዝዮስኮውስኪ፣ ፒዮትር ዚልንስኪ፣ ሮበርት ሊቫንዶውስኪ

ሴኔጋል: ክሃዲም ንዳዬ፣ ላሚኔ ጋሳም፣ ካራ ምቦጂ፣ ካሊዱ ኩሊባሊ፣ ዩሱፍ ሳባልይ፣ ፓፔ አሊዩኔ ንዳዬ፣ ቺኩ ኮያቴ፣ ጋና ኢድሪሳ ጉዬ፣ ኪየታ ባልዴ፣ ምባዬ ኒያንግ፣ ሳዲዮ ማኔ

ይህን ያውቃሉ?

ሴኔጋላዊው የ42 ዓመቱ አሰልጣኝ አሊዩ ሲሴ የዚህ ዓለም ዋንጫ በዕድሜ ትንሽ አሰልጣኝ ነው።