ዓለም ዋንጫ | ፓርቱጋል ከ ሞሮኮ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

ሁለቱ ቡድኖች በሁለት ተቃራኒ ስሜቶች ውስጥ ሆነው ይህን የምድብ ለ ሁለተኛ ዙር ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

ፓርቱጋል ከጎረቤቷ ስፔን ጋር 3ለ3 በተለያየችበት የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ ሃትሪክ በመስራት ድንቅ ብቃቱን ያሳየውን ክርስቲያኖ ሮናልዶን ይዛ ይህን ጨዋታ የምታደርግ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ በመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ በቀዳሚው ጨዋታዋ በመጠናቀቂያ ሰዓት በአዚዝ ቡሃዶዝ አማካኝነት በራሷ ላይ ግብ አስቆጥራ በኢራን ሽንፈት የደረሰባት ሞሮኮ ስህተቷን አርማ ከዚህ ጨዋታ መልካም ውጤት የመያዝ እና የቀደመ ታሪኳን የመድገም ተስፋን ሰንቃ ይህን ጨዋታ የምታደርግ ይሆናል።

የአትላስ አንበሶቹ በአምስት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ ካደረጓቸው 14 ጨዋታዎች (ይህን የዓለም ዋንጫ ጨምሮ) ማሸነፍ የቻሉት በሁለቱ ብቻ ነው። ከእነዚህ ድሎች መካከል ደግሞ ፓርቱጋልን በ1986ቱ የሜክሲኮ ዓለም ዋንጫ ላይ መርታት የቻሉበት ጨዋታ ነው።

ግምታዊ አሰላለፎች

ፓርቱጋል: ሪይ ፓትሪሲዮ፣ ሴድሪክ፣ ፔፔ፣ ጆሴ ፎንቴ፣ ራፋኤል ጎሬሮ፣ ዊሊያም፣ ጁኣ ሞቲንሆ፣ በርናርዶ ሲልቫ፣ ጆኣ ማሪዮ፣ አንድሬ ሲልቫ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ

ሞሮኮ: ሞኒር ኤል ካጁ፣ አችራፍ ሃኪም፣ ጋነም ሳኢስ፣ መኽዲ ቤናሺያ፣ ሃምዛ ሜንድሊ፣ ካሪም ኤል አህማዲ፣ ሃኪም ዚያች፣ ምባርክ ቦሱፍ፣ ዮነስ ቤልሃንዳ፣ ኑረዲን አምራባት፣ ካህሊድ ቦታይብ

ይህን ያውቃሉ ?

ከሩሲያው የ2018 ዓለም ዋንጫ የሞሮኮ የተጫዋቾች ስብስብ መካከል ሞሮኮ በ1986ቱ የሜክሲኮ የዓለም ዋንጫ ፓርቱጋልን ስትረታ ወደዚህች ምድር ማምጣት ችለው የነበሩት 4 ብቻ ናቸው። እነዚህም ምባርክ ቦሱፍ፣ ካሪም ኤል አህማዲ፣ ናቢል ዲራር እና ማኑኤል ዳ ኮስታ ሲሆኑ በወቅቱም ዕድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች ነበር። በጨዋታው ሞሮኮ ፓርቱጋልን 3ለ1 መርታት ችላ ነበር።

ሌሎች የዛሬ የጨዋታ መርሃግብሮች…

Advertisements