አለም ዋንጫ – የበርገር ኪንግ እና የራሺያ ሴቶች ፍጥጫ!


በራሺያ ቅርንጫፍ ከፍቶ እየሰራ የሚገኘው ታዋቂው የአለማችን የፈጣን ምግቦች አቅራቢ የሆነው በርገር ኪንግ ሰሞኑን የሰራው ማስታወቂያ እጅም በጣም አሳፋሪ እና መነጋጋሪያ ሆኖ ቀጥሏል።

ተቋሙ በራሺያ አለም ዋንጫን ለመከታተል ለታደሙ እንግዶች እንደ በርገር አይነት ታዋቂ ፈጣን ምግቦቹን በስፋት እየሸጠ ይገኛል።

ከሰሞኑን በርገር ጊንግ በራሺያው ይፋዊ ገፁ ላይ የሴቶችን መብት እና ክብርን ዝቅ የሚያደርግ ማስታወቂያ ለቆ ታይቷል።

ማስታወቂያው እንዲህ ይነበባል”በርገር ኪንግ ባለበት የማህበራዊ ሀላፊነት ሴቶችን ለመሸለም ተዘጋጅቷል።በአለም ዋንጫው በሚጫወቱ ተጫዋቾች ያረገዙ እያንዳንዱ የራሺያ ሴቶች 35ሺ ፓውንድ እና የእድሜ ልክ የበርገር ኪንግ አገልግሎትን ያገኛሉ።

“እነዚህ ሴቶች ምርጥ የእግርኳስ ባለቤት ያለው ተጫዋች የመውለድ እድል ይኖራቸዋል፣ይህ ደግሞ የራሺያን እግርኳስ በቀጣዩ ትውልድ ውጤታማ እንዲሆን መሰረት ይሆናል።ጉዞ ወደፊት! በናንተ እምነት አለን።”የሚል ነበር።

እንግዲህ በርገር ኪንግ ማህበራዊ ሀላፊነት አለብኝ ብሎ የጠቀሰው የራሺያ እግርኳስ ለወደፊት ውጤታማ እንዲሆን ሴቶች ከኳስ ተጫዋቾች ውለዱ፣ይህን ላደረገ ሽልማቱን ለኔ ተውት የሚል ነው።

ይህ የበርገር ጊንግ ማስታወቂያ ታዲያ በስፋት ትችትን ያስተናገደ ሲሆን ተቋሙም ስህተቱን በመረዳት ማስታወቂያውን በማጥፋት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ አስገድዶታል።

ነገርግን የሴቶች መብት ተሟጋቾች ጉዳዩ በይቅርታ ብቻ የሚቀበሉት አይመስልም።ከበርገር ኪንግ ጋር ተፋጠዋል።

የመላው ሴቶችን ክብር ዝቅ ያደረገውን ተቋም ጉዳይ ወደ ህግ ሊያቀርቡት አስበዋል።

Advertisements