የአለም ዋንጫ – ለሊዮ ሜሲ ፍቅር ብሎ እራሱን አሳልፎ የሰጠው ህንዳዊ!

ዲኑ አሌክስ

አንዳንድ ጊዜ እግርኳስ ከመዝናኛነቱ አልፎ ከልክ በላይ የሆነ ደስታና ሀዘን ስሜትን ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዳይወስድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

በዚህ የራሺያ የአለም ዋንጫም ከሰሞኑን ከተሰሙ አስደንጋጭ ነገሮች ውስጥም የህንዳዊው የሊዮ ሜሲ የልብ ደጋፊ ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል።

ዲኑ አሌክስ ይባላል፣የ30 አመት ህንዳዊ ሲሆን የሚኖረው ደግሞ ኪራላ በምትባል ከተማ ውስጥ ነበር።

ይህ ደጋፊ ለሜሲ እና ለአርጀንቲና ያለው ፍቅር ከልክ ያለፈ እንደነበር በአካባቢው የሚኖሩ ጓደኞቹ ይመሰክሩለታል።

የአለም ዋንጫው ስኬትም ሊዮ ሜሲ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር እንደሚያጣጥም በማሰብ ውድድሩን በታላቅ ጉጉት መከታተል ጀምሯል።

የአልባሴቴዎቹ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ግን እንዳሰባቸው ሳይሆኑ ከአይሳላንድ ጋር 1-1 በመቀጠል ደግሞ በክሮሺያ አስደንጋጭ የ 3-0 ሽንፈት ገጠማቸው።

ህንዳዊው ዲኑ አሌክስ በንዴት የተንቀለቀለው ስሜቱን መቆጣጠር አልቻለም፣የአርጀንቲና ተስፋ ያበቃለት ስለመሰለው ወደ ቤቱ በማቅናት ይህን ማስታወሻ አሰፈረ።

“በዚህ ምድር ላይ የቀረኝ ነገር የለም።አሁን ወደማልመለስበት ቦታ ሄጃለው።በኔ ሞት ማንም ተጠያቂ አይደለም።ሜሲ …ህይወቴን ላንተ ሰጥቼ ነበር፣የአለም ዋንጫም ታነሳለህ ብዮ አስቤ ነበር።”በማለት አሰፍሮ ከቤቱ ወጣ።

ከአንድ ቀን በኋላ በከተማው የሚገኝ ወንዝ ውስጥ የሞተ ሰው ተገኘ።ፓሊስ ባደረገው ምርመራም ሟች ህንዳዊው ዲኑ አሌክስ ነበር።

Advertisements