የአለም ዋንጫ -የጃፓኖቹ መልእክት “спасибо”  

ጃፓኖቹ በቤልጄም ከተሸነፉ በኋላ በመልበሻ ቤታቸው ያልታሰበ ተግባር ፈፅመዋል።

የጃፓን ብሔራዊ ቡድን በአሳዛኝ ሁኔታ በቤልጄም ተሸንፈው ከአለም ዋንጫው ወደ ሀገራቸው ቢመለሱም ለሁሉም ቡድኖች ምሳሌ ሊሆን በሚችለው ተግባራቸው እየተወደሱ ይገኛሉ።

በ25 ደቂቃ ውስጥ በተቆጠረባቸው ሶስት ጎሎች ከውድድሩ ሲሰናበቱ ከጨዋታው በኋላ ደጋፊዎቹ ስታድየሙን አፅድተው መውጣታቸው ሳያንስ ተጫዋቾቹ ደግሞ በመልበሻ ቤታቸው ይህንኑ መልካም ስራ ደግመውታል።

ተጫዋቾቹ የጨዋታው ንዴት ሳይበግራቸው መልበሻ ቤታቸውን መስታወት እስኪመስል[ምስሉን ይመልከቱ] አፅድተው ወጥተዋል።

ይበልጥ የሚገርመው ደግሞ በመልበሻ ቤቱ ፊትለፊት ላይ በራሺኛ “спасибо” የሚል ፅሁፍ ለጥፈው መሄዳቸው ነው።ትርጉሙም እናመሰግናለን የሚል ነው።

የጃፓኖቹ ደጋፊዎች መልካም ተግባር የሌሎች ቡድኖች ደጋፊዎችም እየተጋሯቸው ይገኛሉ።

በምድብ ጨዋታ ላይ ሴኔጋሎች ተመሳሳይ ነገር የፈፀሙ ሲሆን ትናንት ደግሞ የክሮሺያ ደጋፊዎች ራሺያን ካሸነፉ በኋላ የጃፓኖቹን ፈለግ ተከትለዋል።

Advertisements