የአለም ዋንጫ – በሜሲ እና ሮናልዶ ክርክር የተፋቱት ጥንዶች

ጥንዶቹ ሜሲ ይበልጥ ፣ሮናልዶ ክርክራቸው በትዳር የገነቡትን ፍቅራቸው እና የጋብቻ ማስረጃቸውን ቀደው ለመፋታት ደርሰዋል።

ሉዩድሚላ እና አርሴን ጃፓን እና ኮሪያ ባዘጋጁት የ2002 የአለም ዋንጫ ላይ በአንድ መጠጥ ቤት ውድድሩን ሲመለከቱ ነበር የተዋወቁት።

እነዚህ ራሺያዊ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ፍቅራቸው ደምቆ እና አብቦ ባለፉት ረጅም አመታት በትዳር ተሳስረው ቆይተዋል።

በሁለቱ ጥንዶች መካከል የነበረው ልዩነት ግን ሚስት አርሴን የክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ባል ልዩድሚላ ደግሞ የሊዮ ሜሲ አድናቂ መሆናቸው ነበር።

ነገርግን ሜሲ ይበልጥ ክርስቲያኖ … ክርክራቸው ከራሺያው የአለም ዋንጫ ሳያሻግራቸው ለመለያየት በቅተዋል።

“የአለም ዋንጫው ከተጀመረ ጀምሮ በሜሲ ላይ ታፌዛለች፣የፍፁም ቅጣት ምት እንኳን አይስላንድ ላይ ማግባት የማይችል እያለች ተናግራለች፣እኔ ግን ለሮኖልዶ ያለኝ ስሜት እና ስለምትወደው ክለብ አውርቼ አላውቅም።”በማለት ባል ተናግሯል።

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ አርጀንቲና ናይጄሪያን ካሸነፈች በኋላ ሚስት አርሴን የፍቺ ደብዳቤ ለፍርድቤት አስገብታ ጥንዶቹ መለያየታቸው ነው።

Advertisements